tg-me.com/nibab_lehiwot/150
Last Update:
🕊️ሀሙስ 🕊️
ክፍል-5
አውቃለሁ........ ሊያምሽ ይችላል አወ እንዲያምሽ ነው ምፈልገው ለመዳን የግድ በደምብ መታመም አለብሽ።......ንግግሩ መላ ሰውነቴን ይሰረስረው ጀመር።ምንም ሳላስብበት እንባ ከአይኖቸ ለመውጣት ያቆጠቁጥ ጀመር።ልቤን የሆነ ነገር የወጋኝ ያህል አመመኝ።
ምንም ቃል ለመናገር አንደበቴ እምቢ አለኝ። አ.....አዎ ልክ ነወት እኔስ ኢትዮጵያዊ የሚለው ክብር አይገባኝም ብየ በሁለት እጆቸ አይኖቸን ጠራረግኩ።እንባየ ግን አልቆመም።
አሁን ማልቀስ መፍትሔ አይሆንም ከተኛሽበት ንቂ።አሁን በድጋሚ ልጠይቅሽ ኢትዮጵያዊ መሆን አትመኝም ?
......... በደምብ ነው ምፈልገው አልኩዋቸው ከልብ በሆነ ስሜት....
እ አባባ አንድ ጥያቄ መጠየቅ እችላለሁ አልኩ እንዳቀረቀርኩ።
አዎ ጠይቂኝ ከመጠየቅ ነው ጥበብ ሚገኘው እግዜርስ ጠይቁ ይሰጣችሁማል አይደል ያለው .............ዝም ብለሽ የነገሩሽን ከማመን ጠይቂ መጠየቅ ጠቢብ ያደርጋል።
እሽ ግን ለምን ይሄ ሁሉ ታሪክ እያለን ፣ሁሉም ነገር የኛ ሆኖ እያለ ፣ጥበብ ሁሉ ተሰጥቶን .......
ለምን ተሰወራችሁብን ፣ለምን ግልፁን አትነግሩንም ፣ ለምን ዝምታን መረጣችሁ አልኩት........
✍bee
BY ሕይወትን - በገፅ
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 283
Share with your friend now:
tg-me.com/nibab_lehiwot/150